Citizen Charter

የሜኒሶታ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር ይዘት


 1.   የቻርተሩ ዓላማ

 • የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት ማረጋረጥ፤
 • ለዜጎች ጥራት ያለው አገልግሎት ለመሰጠት፤
 • ተጠያቂነትን በግልጽ ለማመልከት፤
 • ዜጎች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ፍጥነት፣ በምን የጥራት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፤

2.   የጽ/ቤቱ ራዕይ

 • በበጀት ዓመቱ ከትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እና ሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን አገራችን ከአሜሪካ አገር ጋር ያላትን የቢዝነስና የኢኮኖሚ ግንኙነት ለማጠናከርና ለዜጎቹ የላቀ የኮንስለር አገልግሎት የሚሰጥ ጽ/ቤት መሆን፣

3.   የጽ/ቤቱ ተልእኮ

 • “ቀጣይና አሰተማማኝ ተቋማዊ የለውጥ ስርዓት በመዘርጋት፤ የልማት ትግላችንን የሚያሳካ፤ የሰላም ስጋቶችን የሚያስወግድና ለልማት የተመቻች ሁኔታን የሚፈጥር፤ መልካም ገጽታን የሚገነባ፤ የዲያስፖራ ተሳትፎን የሚያሳድግና ጥቅምን የሚስጠብቅ ዲፕሎማሲ ማራመድ”

4.   የጽ/ቤቱ ዕሴቶች

 • የሕዝብ አገልጋይነት –  Public Service
 • አጋርነት – Partnership
 • ተዓማኒነት – Integrity
 • ቁርጠኝነት – Commitment
 • ግልጸኝነት – Transparency
 • ውጤታማነት – Effectiveness ናቸው።

5.   የእሴቶች መግለጫ


5.1.  የሕዝብ አገልጋይነት (Pbblic Service)

 •   ዜጎቻችንና ባለድርሻ አካላትን በከፍተኛ ትህትና፡ ቅንነትና ቅልጥፍና ማገልገል ኃላፊነታችንና ግድታችን ነው። ይህም በየዕለቱ በምናደርገው ዲፕሎማሲያዊ ተግባራችን ይገለፃል። ይህ እሴታችን ደንበኞቻችንና ተጠቃሚዎች በምናስገኘው የእርካታ መጠን፤ እንዲሁም እያንዳንዱን አገልግሎት ለመሰጠት ከወሰድነው ጊዜና ጥራት አንፃር የሚለካና በዕለት ተዕለት እንቅስቃስያችን ውሰጥ ተግናራዊ የሚደረግ ይሆናል።

     5.2.  አጋርነት (Partnership)

 • እንደተቋምና እንደግለሰብ የመ/ቤቱን ተልዕኮና ራዕይ በተሳካ ሁኔታ ተግማራዊ ለማድረግ የተቋሙ ሠራተኞች እርስ በርሳችን፤ እንዲሁም ከልሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ሰካላትና የልማት ጋሮች ጋር በምንፈጥረው ወዳጅትና የተቀናጅ አሰራር አጋርነትን እናጎለብታለን። አጋርነት የዕለት ተዕለት ሥራችን መገለጫ ሲሆን ይህም የመ/ቤቱን ራዕይ እና ተልዕኮ በማሳካት ሂደት ባፈራናቸው አጋሮች ብዛት የሚለካ ዕሴት ነው።

5.3.   ተዓማኒነት (Integrity)

 • ለመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራትጂዎች ጥብቅና በመቆም በታማኝነትና በቁርጠኝነት መፈፀም፤ የሀገርንና የዝባችን ጥቅም በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ማሰጠነቅ እንዲሁም የአገርንና የተቋሙን ምስጢሮች መጠበቅ፤ ከአድልዎ የፀዳ ግልጽ አሠራር መዘርጋት፤ ፍትሐዊነት፤ ቅንነት፤ ግልጽነትና ተጠታቂነትን በሚያረጋግጥ አኳኃን የተቋሙን ተልዕኮና ኃላፊነት በብቃትና ውጤታማነት መወጣትን ይመለከታል። ይህም ይተቋሙን የሥራ ዕቅዶችና ግቦችን ከመተግበርና ከማሳካት አኳያ የሚለካ ይሆናል፡

       5.4.   ቁርጠኝነት

 •  ፈጣን ልማት ለማረጋገጥ፤ ኪሞከራሲዊ ሰረዓት ለመገንባትና የአገራችንን ደህንነትና ሠላም ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መነሳሳት ወሣኝ ነው። በመሆኑም ተቋማዊ ኃላፊነታችንን ለመግለጽ በየደረጃ ለሚካሄድ የዲፕሎማሲ ሥራ ቁርጠኛ አቋም መያዝ ከሁሉም የሚጠበቅ እሴት ነው።

       5.5.     ውጥታማነት (Effectiveness)


 • የዲፕሎማሲ ሥራችንንና አሰልግሎት አሰጣጣችን በቅልጥፍና ከመስራት በሻገር ሥራዎቻችንና አገልግሎቶቻችን ጥቅም የሚሰጡና ውጤት የሚያስመዘግቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

6.   ተገልጋዮች

 • የውጭ ዜጎች፤
 • የውስጥ ሠራተኞች፣
 • በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊናንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፤
 • በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋሙ የኢትዮጵያ ህዳሴ ምክር ቤቶች፣ የልማት፤ የሙያ፤ የቢዝነስና ሌሎች ማህበራት፤
 • በውጭ ያሉ የሃይማኖት ድርጅቶች
 • የኢትጵያውን የተያዙ ቱር ኦፕሬተሮች፤

7.  አጠቃላይ መርሆዎች

 • ቀልጣፋ፤ ጥራት ያለው ፤ ውጤታማና አስተማማኝ የመረጃ አገልግሎት እንሰጣለን፤
 • ቀልጣፋ፤ ጥራት ያለውና ውጤታማ፤ የፓሰወፖርትና ቪዛ፤ የሠነድ ማረጋገጥና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ፈጣን የፕሮቶኮል አገልግሎት እንሰጣለን፤
 • ላሰቀመጥናቸው እሴቶች እንገዛለን፤
 • ለዜጎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ፈጣን መልስ እንሰጣለን፤
 • ከአድሏዊ አሰራርና ከሥነ-ምግናር ጉድለት የፀዳ አሰራርን እንከትላለን፤
 • ለሰጠናቸው አገልግሎቶችና ለወሰናቸው ዉሳኔዎች ተጠያቂዎች ነን፤

8.   የተገልጋዮች መብቶች

 • በጽ/ቤቱ የሚሰጡትን አሰልግሎቶች የመጠየቅና የማገኘት፤
 • የተሟላ መረጃ የማግኘት፤
 • በፍጥነትና በቅልጥፍና የመሰተናገድ፤
 • የተሰጣቸውን አገልግሎት በተመለከተ አስተያየት የመሰጠት፤
 • ባልተገናኘ አገልግሎት ቅሬታዎቻቸውን በየደረጃው የማሰማትና ለቅሬታዎቻቸው ምላሽ የማግኘት፤

9.  ከተገልጋዮች የሚጠበቅ ግድታ

 • ትክክለኛና ታማኝነት የሆነ መረጃ አሟልቶ ማቅረብ፡
 • ታማኝነት፤
 • በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ አሰተያየት መሰጠት፤

10.   ከጽ/ቤት የሚጠበቁ ስኬቶች (Outcomes)

 • የተፈጠረ ጠንካራ የዳያሰፖራ ትስስር፤
 • በቢዚነስ ፍሰት የተገኘ ተጨማሪ የውጭ ሀብት፤
 • ለልማት፤ ሰላምና ኪሞድራሲ ስረዓት ግንባታ የተመቻቸ የውጭ ሁኔታ፤
 • የተገነባ የሀገር ገጽታና የተበራከቱ ደጋፊዎች፤
 • የተደረገ የትክኖሎጂ ሽግግር
ተ.ቁየሚሰጡ አገልግሎቶችአገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታየአገልገሎት አሰጣጥ ሰታንደርድአገልግሎቱን ለማገኘት የሚጠየቅ ቅድመ ሁኔታ
ጊዜጥራትብዛት